Saturday, November 29, 2014

የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የወር በጀታቸው በዩኒቨርሲቲው ሃላፊዎች መጠፋፋቱ ተገለፀ።



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያለፈው ወር በጀታቸው በሃላፊዎቹ እንደተጠፋፋ የገለፀው መረጃው በዚህ መሰረትም ተማሪዎቹ በጀታችንን ሳንጠቀምበት በሃላፊዎቹ ስለተጠፋፋ ለከባድ ማህበራዊ ችግር ተጋልጣናል በማለት ከባድ ተቃውሞ እንዳካሄዱ ታውቋል።
    መረጃው ጨምሮ የዩኢቨርሲቲው አመራሮች የተነሳውን ተቃውሞ ከተማሪዎቹ ጋር ተመካክረው መፍታት ስላልቻሉ የስርዓቱ ፌደራል ፖሊሶች ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ዘልቀው በመግባት በሃይል እንዳስቆሙት ለማወቅ ተችሏል።
     በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚከሰተው ተደጋጋሚ የበጀት መጠፋፋት ምክንያት በተማሪዎቹ ማህበራዊ ህይወት ላይ ችግር እያጋጠመ መምጣቱን ባለፈው የዜና እወጃችን መገለፁ ይታወቃል።