Saturday, November 29, 2014

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን የዕለት ስራቸውን ለማሳለጥ ከቦታ ወደ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የነበሩ ንፁሃን ዜጎች በፌደራል ፖሊስ ታፍነው እንደተወሰዱ ተገለፀ።



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት ከሁመራ ወደ ዲማ በሚወስደው መንገድ ላይ ህዳር 5/2007 ዓ/ም የግል ስራቸውን ለማሳለጥ በእግራቸው ሲጓዙ የነበሩት በለጠ ገብረሂወት የተባለ ግለሰብ የሚገኝባቸው አምስት ንፁሃን ዜጎቻችን የፈፀሙት ወንጀል ሳይኖራቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገድ ላይ ጠብቀው አፍነው እንድወስዷቸው ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው እነዚህ ዜጎች ሰርተው ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከማስተዳደር ውጭ ምንም አይነት ችግር እንዳልነበራቸው በአካባቢው ህብረተሰብ የሚታወቁ እንደሆኑ የገለፀው መረጃው በፌደራል ፖሊስ ታፍነው እንደተወሰዱ ያወቁት ቤተስቦቻቸው ሁኔታቸውን ለማረጋገጥ ሲሉ። ይመለከታቸዋል የተባሉትን አካላት ቢጠይቁም እስካሁን ግን የት እንዳሉ ማወቅ እንዳልቻሉ ታውቋል።