Saturday, November 22, 2014

የአንድነት ተቃዋሚ ድርጅት በዚህ ሳምንት በዳንሻና አካባቢው ያደረገው ቅስቀሳ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት በማግኘቱ የሰጉ የስርዓቱ ካድሬዎች ሰዎችን የማፈን ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በትግራይ ምዕራባዊ ዞን በዳንሻ ልዩ ስሙ ሜይዴይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚታገለው የአንድነት ፓርቲ በዚህ ሳምንት ህዝብ ሰብሰቦ ባካሄደው ሰፊ ቅስቀሳ የህዝብ ተቀባይነት ያገኛል የሚል ጭፍን አስተሳሰብ ያደረባቸው የስርዓቱ  አስተዳዳሪዎች በአንድነት ተቃዋሚ ድርጅት ስብሰባ ላይ ይተባበራሉ እንዲሁም በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ሰዎች በማፈንና በማሰር ተግባር ላይ እንደተሰማሩ ለማወቅ ተችሏል።
   በስልጣን ላይ የሚገኘው ገዥው መንግስት ዲሞክራሲያዊ ለመምሰል ስብሰባ እንዲካሄድ ካደረገ በኋላ ያሰጋሉና ለተቃዋሚዎች ይተጋገዛሉ ያላቸውን ሰዎች በማሰርና በማፈን  ስራ ላይ መሰማራቱን የገለፀው መረጃው ጥቅምት 25 /2007 ዓ/ም ከታፈኑት የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል መሰለ ደጀኔ፥ ባህታ ደመቀና ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የአርማጭሆ ተወላጅ የሚገኙባቸው የገዥው ቡድን አስተዳዳሪዎች ባሰማሯቸው የፀጥታ አካላት ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ አድራሻቸው እንዳልታወቀ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።