Saturday, November 22, 2014

የተምቤን ዓብይ-ዓዲ ከተማ ወጣቶች ወደ ውትድርና እንዲገቡ በጉጅሌው የኢህአዴግ ካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ ህብረተሰቡ እንዳልተቀበለው ምንጮቻችን ገለፁ።



    በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን የተምቤን ዓብይ-ዓዲ ከተማ ጥቅምት 3 /2007 ዓ.ም በኢህአዴግ ባለ-ስልጣኖች ስብሰባ እንደተካሄደ የገለፀው ይህ መረጃ የስብሰባው አጀንዳም በመከላከያ ያለው የትግራይ ብሄር ተወላጅ በቁጥር ያነሰ ስለሆነ ወጣቶቹ ወደ ውትድርና እንዲገቡ የሚቀሰቅስ እንደነበር ተገልጿል።
     መረጃው በማስከተል በስርዓቱ ካድሬዎች ለቀረበው ወጣቶቹ ወደ ውትድርና እንዲገቡ የሚጠይቀውን አጀንዳ ተሰብሳቢው ማህበረሰብ ከዚህ በፊት ታግለን ምን አገኘን ውጤቱ ኪሳራና ጉዳት ነው፣ ስለዚህ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ጥፋት አንገባም ልጆቻችንንም አንሰጥም በማለት በአንድ ድምፅ ተቃውሞአቸውን እንዳሰሙ ለማወቅ ተችሏል።
     በተመሳሳይ በሁመራ ከተማ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች የኢህአዴግ ካድሬዎች ሰብስበው ወደ ውትድርና እንዲሰለፉ ጥቅምት 24/2007 ዓ.ም ቅስቀሳ እንዳካሄዱላቸውና ይህ ተግባር  ደግሞ በሃገር ደረጃ እየተካሄደ ያለ ቅስቀሳ  ቢሆንም በህዝብ ዘንድ ግን ተቀባይነት ማግኘት እንዳልቻለ ከዚህ በፊት በዜና እወጃችን መግለፃችን ይታወሳል።