Tuesday, November 18, 2014

በትግራይ ክልል የባድመ ተወላጆች በሰፈራ ስም ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖቻችን ቤተሰብ ለመጠየቅ በሚመጡበት ሰዓት። ከተቃዋሚዎች ጋር ለመገናኘት ነው የመጣችሁ እየተባሉ በወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት እየተጠለፉ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስታውቁ፣




     በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በትግራይ ክልል ሰሜናዊ  ምዕራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ  የባድመ አካባቢ ተወላጅ የሆኑ ወገኖቻችን። ባለፉት አመታት የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት  ችግራችሁን ትፈታላችሁ በማለት ከመኖርያ ቀየአቸው በማፈናቀል እድሪስ ወደተባለው አካባቢ ወስዶ እንዳሰፈራቸው የገለፀው መረጃው። እነዚህ ሰዎች ከሚኖሩበት ቦታ  ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ዘመዶቻቸው በሚመለሱበት ሰዓት። ከተቃዋሚዎች ጋር ልትገናኙ ነው የመጣችሁ ተብለው በስርዓቱ አስተዳዳሪዎች እና በፀጥታ ሃይሎች ታፍነው እንደተወሰዱ ሊታወቅ ተችሏል፣
     ይህ በእንዲህ እንዳለ። ለብዙ ጊዚያቶች ከቤተሰቦቻቸውና ከዘመዶቻቸው ተለይተው የቆዩ ወገኖች የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት ለመጠየቅ በመምጣታቸው ብቻ። በስርዓቱ የመጠለፍ አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ተክለማርያም አሰፋ የተባለ እንደሚገኝባቸውና ቤተሰቦቻቸውም እስካሁን ድረስ የት እንዳሉ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል፣