Tuesday, November 18, 2014

የህወሓት ኢህአደግ ባለስልጣናት በክልል ደርጃ የቀበሌ ፤ የወረዳና የዞኖች ኣስተዳዳሪዎች የተሳተፉበት ስብሰባ ላይ። ህዝቡ ተቃውሞ እንዳያስነሳ ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ ቢያሳስቡም ተቀባይነት እንዳላገኙ ተገለፀ፣




       በስብሰባው የተሳተፉት ምንጮቻችን እንደገለፁት። በከፍተኛ  የህወሓት-ኢህአዴግ ቡድን አመራሮች እየተከናወነ ያለው ስብሰባ። እንደ ዋነኛ አጀንዳቸው አድርገው የያዙትም። እናንተ አዲሱ ትውልድ ስለሆናችሁ ስልጣን የናንተ ነው እንዲሁም ህዝቡ ፀረ ህወሓት-ኢህአደግ ተቃውም እንዳያስነሳና በተቃዋሚዎች የሚቀርብ ምርጫን የሚመለከት ቅስቀሳ  ህዝቡ እንዳይሰማ ብሎም  እንዳይደግፋቸው በቅርብ ሆናችሁ እንድትከታተሉ የሚል እንደነበረና በተሰብሳቢዎች ግን ተቀባይነት እንዳላገኘ ታወቀ፣
      መረጃው በማስከተል። ተሰብሳቢዎች ካቀረቡት ሃሳብ ለመጥቀስ ያህል። መንግስት ከህዝቡ ጋር ሳይረዳዳ ተገቢውን የካሳ ክፍያና ተለዋጭ መሬት ሳይሰጥ  ቤቶችን በተደጋጋሚ ማፍረሱና በህዝቡ የተመረጡ ሰዎችን ትታችሁ ራሳችሁ የመረጣችሁትን ሰው በአመራር ላይ ማስቀመጣችሁና በሌሎችም ግድፈቶች ምክንያት ህዝቡ ጠልቷችኋል፤  አሁን በህዝብ ስለተጠላችሁ ነው ስልጣን  ተረከቡን የምትሉን እስካሁን  የት ቆይታችሁ ነው? ይህንም ደግሞ ለይስሙላ አትናገሩን። በማለት እንደተቃዋሟቸው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣