Friday, November 7, 2014

የኢህአዴግ ገዥው ስርአት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚኖር ህዝብ ከፋፍለው እያካሄዱት የሰነበቱት ስብሰባ ተቀባይነት እንዳላገኙበት ተገለፀ፣




   የኢህአዴግ ስርዓት በግንቦት ወር ለሚካሄደው የይስሙላ ምርጫ መሰረት ያደረገ በሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ  ከተሞች የወጣቶች፤ የሃይማንኖቶች፤ የሃገር ሹማግሌዎች ወዘተ በማለት በጉጅሌ ከፋፍሎ ሲያካሄደው በሰነበተው ስብሰባ ላይ ደጋፊ ለማግኘት ታልሞ የተካሄደ እንደነበረና፤ በአንፃሩ ግን ህብረተሰቡ ሊቀበለው እንዳልቻለ ስብሰባው ላይ የተካፈሉት ምንጮቻችን አስታውቁ፣
       ስርዓቱ እያካሄደው ባለው እኩይ ተግባር ያልተደሰተው የአዲስ አበባ ማህበረሰብ፤ “እስካሁን ሳትመረጡ ለ20 አመት ያህል በስልጣን ተቀምጣችሁ ምንም አይነት ለውጥ አላመጣችሁም። ስለዚ አሁን እያደረጋችሁት ያላችሁት ስብሰባ ህብረተሰቡን ለማደናገር እንጂ ለህዝብ አዝናችሁ አይደለም። እስካሁን የተሸከምናችሁ ይበቃችኋል። ምርጫን በሚመለከት ከናንተ ጋር የምንነጋገርበት ምንም አይነት መንገድ የለንም። ማንን እንደምንመርጥ እኛ እናውቃለን።” በማለት እንደተቃወሙት የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል፣