Friday, November 7, 2014

በቃፍታ ሁመራ ወረዳ የአስተዳዳሪዎችን አሉባልታ የተቃወሙ ንፁሃን ዜጎቻችን በሌሊት እየታፈኑ በመታሰር ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አስታወቁ፣




    በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ የትርካን ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ መብራህቱ ሃይለና፤ ታደሰ ዳርግሊኝ የተባሉ ወገኖች ጥቅምት 12/ 2007 ዓ,ም ከለሊቱ ሶስት ሰዓት ላይ ታፍነው መወሰዳቸውና፤ የነዚህ የታፈኑት ቤተሰቦች  የታሰሩበትን ቦታ ስለማያውቁ፤ ወንድሞቻችን እየተጠለፉ በመጥፋት ላይ ናቸው በማለት እስከ ዞን ድረስ በመሄድ አቤቱታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችችን አስታውቀዋል፣
    የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ህብረተሰቡ እያሳየው ባለው ከፍተኛ ምሬት፤ ተቃውሞ እንዳያስነሳ ስለሰጉ፤ እነዚህ የተጠለፉ እስረኞች ወደ ሁመራ መጥተው እንደታሰሩ ከገለፁ በኋላ፤ ቤተሰቦቻቸው ምን አድርገው ነው ሊታሰሩ የቻሉት ብለው ቢጠይቁም ተገቢ መልስ ስላልተሰጣቸው፤ ህብረተሰቡ ግን እነዚህ ሰዎች ተጠልፈው የታሰሩት በተለያዩ ስብሰባዎች እየተነገሩ ያሉትን የስርዓቱ ማደናገርያ ሓሳቦች ትክክል እንዳልሆኑ በመናገራቸው ብቻ፤ ረዳት ኢንስፔክተር ሓዱሽ አርአያ በተባለ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ ታስረው እንደሚገኙ ህዝቡም በሰፊው እየተነጋገረበት እንደሚገኝ ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል፣