Friday, November 7, 2014

በአዲጎሹና አካባቢው የሚገኙ ገበሬዎች ያፈሩትን ምርት በአስተዳዳሪዎች እየተቀሙ እንደሚገኙ ተገለፀ፣




   በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ዓዲ ጎሹ አካባቢ ሰሊጥ ዘርተው የከረሙ ገበሬዎች ምርታቸው እያስገቡ ባሉበት ሰዓት የዞኑና የወረዳው አስተዳዳሪዎች ያልተፈቀደላችሁ መሬት አርሳችኋል በሚል ምክንያት ታማኝ ካድሬዎቻቸውንና አባሎቻቸውን አስማርተው እስካሁን 1.300 ኩንታል ሰሊጥ ቀምተው እንደወሰዱ ሊታወቅ ተችሏል፣
የሰሊጥ ምርታቸው ከተቀሙት ውስጥ የተወሰኑትን ለመጥቀስ!
·        ተስፋይ ሳህለ የዓዲጎሹ ነዋሪ =  40 ኩንታል
·        የኔሁን ገብረኪዳን የዓዲጎሹ ነዋሪ = 55 ኩንታል
·        ገብረስላሰ ሃፍቱ የማይትሩቤል ነዋሪ =  30 ኩንታል
·        ፀጋይ ግደይ የማትረብየል ነዋሪ = 35 ኩንታል ሰሊጥ እንደተወሰደባቸው ለማወቅ ትችሏል፣
    በተመሳሳይ የ2006 እና የ2007 ዓ.ም የምርት ዘመን በበረኸት አካባቢ የሚገኙ ወጣቶች የዘሩትን ሰሊጥ እንዳያጭዱት በማለት የወረዳው አስተዳድሪዎች ከጥቅምት 5 /2007 ዓ.ም ጀምረው ሙላት አዳነ፤ ክፍላይ ክፍለ፤ አደራጀው ገብረማርያምና፤ ሊሎችም ስማቸው ለጊዜው ያልተጠቀሱ በርካታ ወጣቶች የሚገኙባቸው በበረኸት ታስረው እንደሚገኙ ከዚህ በፊት በዜና እውጃችን መግለፃችን ይታወሳል፣