Wednesday, November 5, 2014

የአረና ትግራይ ተቃዋሚ ድርጅት በትግራይ ክልል በነፃነት ተንቀሳቅሶ ስራውን ማከናወን እንዳልቻለ ምንጮቻችን የላክሉን መረጃ አስታወቀ፣





ጥቅምት 12/2007 ዓ/ም በላዕላይ አድያቦ ወረዳ አዲ ዳዕሮ ከተማ፤ አየነው በየነ የተባለው የዓረና አባል መሆኑን በሕጋዊ ወረቀት ሲንቀሳቀስ የነበረ ህጋዊ ግለ ሰብ በከተማው ውስጥ የድርጅቱን በራሪ ፅሁፎች እያሰራጨ በነበረበት ሰአት በህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች ተይዞ መታሰሩን ተገለፀ፣
     የኢህአዴግ ገዢ ባለስልጣኖች በያዝነው አመት በሚካሄደው ምርጫ ላይ፤ ህዝቡ ለተቃዋሚዎች እንዳይመርጥ በመስጋታቸው ምክንያት፤ ለሚያሰጉዋቸው ተቃዋሚዎች ከህዝቡ ለመነጠል ሲሉ፤ ባልዋሉበት ወንጀል ክስ በማቅረብ እንዲታሰሩና በላያቸው ላይ ግፍ እንዲፈፀምባቸው እያደረጉ መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ አስታወቀ፣
     በስልጣን ላይ ባለው ስርአት አምስተኛ ግዜ እንዲካሄድ ታስቦ ያለውን አስመሳይ የ2007 ዓ/ም ምርጫ ላይ፤ በሰላማዊና ፖለቲካዊ ትግል ለኢህአዴግ ከስልጣኑ ማስወገድ ይቻላል ብለው ለተነሱ ድርጅቶች ከወዲሁ  ተወዳዳሪነታቸው ከውዲሁ ያቀጨጨ መሆንን በህዝቡ ውስጥ እንደ ዋነኛ መነጋገርያ ነጥብ ሁኖ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ አክሎ አስረድቷል፣