Saturday, December 6, 2014

የትግራይ ህዝብ አስነስቶት ባለው መሰረታዊ ጥያቄ የህወሃት ኢህአዴግ ባለስልጣናት በከባድ ጭንቀት ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ያገኘነው መረጃ ገለፀ።



       ከተለያዩ የትግራይ ክልል የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በከተማና በገጠር የሚኖር ህብረትሰብ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ተመሳሳይ መሆናቸውን የገለፀው ይህ መረጃ ለኢህአዴግ ባለስልጣናት በህብረተሰቡ ከቀረቡት ጥያቄዎች የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል።
·        መልካም አስተዳደር ስለሌለ ህዝብ ከህግ ውጭ በሆነ መንገድ እየታሰረ ይደበደባል!
·        ባለስልጣናት በፍትህ ላይ እጃችሁን በማስገባት እያበላሻችሁት ስለሆነ ዳኞች ህግ በሚደነግገው መሰረት እንዳይሰሩ ተፅእኖ እየፈጠራችሁባቸው ነው!
·        መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአላቂ ነግሮች እጥረት በሚቸገርበት ሰዓት መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ። በአንፃሩ ከአቅም በላይ ግብር እንዲከፍልና ማዳበርያ በውድ ዋጋ እንዲገዛ እያስገደዳችሁና በችግር እየፈጠራችሁ ታስጨንቁት አላችሁ!ይህ ደግሞ አንድ ፀረ ህዝብ ስርዓት የሚከተለው መንገድ ነው የሚሉና ሌሎችንም ያካተተ ጥያቄ እንደነበር ለማወቅ ትችሏል።
       መረጃው ጨምሮ እንደሚያሰረዳው የህወሃት ኢህአዴግ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች ለህዝብ አዛኝ ለመምሰል መድረኮችን እየከፈታችሁ ህዝብ እንዲነቅፍና እንዲናገር ካደረጋችሁ በኋላ፤ ይህ ሰው ንፁህ እያለ ሃሳቡ በመግለፁ ብቻ፤ ምክንያት እየፈጠራችሁ ያለምንም ይዋል ይደር ጠልፋችሁ በመውሰድ ዳብዛውን ታጠፉት አላችሁ የሚሉ ጥያቄዎች በምርጫው ዋዜማ በህብረትሰቡ እየተነሱ በመሆናቸው፤ ለስርዓቱ ካድሬዎችና አመራሮች ከፍተኛ ፈተናዎች ሁነውባቸው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በላኩልን መረጃ ለመረዳት ተችሏል።