እንደምንጮቻችን መረጃ የህወሃት ባለስልጣናት 40ኛ አመታቸውን የካቲት 11 ላይ ለማክበር እየተዘጋጁ ባሉበት ሰዓት በሙዚየሙ ውስጥ ያለው
የተሰው ታጋዮች ስዕል ማንነታቸው ስለማይታወቅ፤ የነዚህ ሰዎች ስምና የታሪክ ማህደራቸው የት አለ? በማለት ህብረተሰቡ በሚጠይቅበት
ሰዓት አንዳንድ የህወሃት አመራሮችና ካድሬዎችም ህዝቡ እያነሳው ካለው ጥያቄ ጋር በመስማማት በህወሃት የተሰውትን የታሪክና የሰነድ
አያያዝ እየጠየቁ መሆናቸውን ለማወቅ ትችሏል።
ከዚህ በመነሳት ደግሞ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፤ የሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችንና
ከዚህ በፊት ታጋይ ለነበሩ በአሁኑ ግዜ የዞን አስተዳዳሪ ሁነው ያሉት፥ ለህዝቡ እባካችሁ የያዛችሁትን ወይ ደግሞ ያገኛችሁት የህወሃት ዶክሜንት ካለ አሁን አስፈላጊ ሁኖ ስለተገኘ ተባበሩን እያሉ እየተየቁ መሆናቸውና
የወረዳ አስተዳዳሪዎችና ህብረተሰቡ ግን አሁን አይደለም ታሪክ የሚጠየቀው!! እስካሁን የት ነበራችሁ? ለምን ቀድመውም በጥሩ ሁኔታ
የማትሰንዱት እያሏቸው እንደሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ አስታውቀ።