Wednesday, December 10, 2014

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን፤ አደባይ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ መሪዎች የተከለከለ ቦታ አርሳችኋል በሚል ምክንያት ነዋሪዎቹ ያፈሩትን ሰብል በእሳት እንዳቃጠሉባቸው ተገለፀ።



   ከቦታው ያገኘነው መረጃ እንዳስረዳው የአደባይ ነዋሪ ህዝብ በተለይ ወጣቱ ትውልድ በእርሻ መሬት እጦት ምክንያት እጅግ መቸገሩንና ወደ አስተዳዳሪዎች አቤቱታ አቅርቦ ሰሚ  ባለማግኘቱ የተነሳ፤ ኑሮውን ለመምራት ሲል ተከልክሎ በነበረው የእርሻ መሬት ላይ እህል በመዝራቱ ምክንያት በላዩ ላይ በደል እንደተፈፀመበት ለማወቅ ተችሏል።
   ለእርሻ የሚውል ሰፊ መሬት እያለ የሚታረስ ቦታ አጥቶ ተቸግሮ ያለው የአካባቢው እርሶ አደር በቁሜ እያለሁ ለረሀብ አልጋለጥም በማለት ለእርሻ የሚሆን መሬት መንጥሮ በመጠቀሙ ብቻ፤ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች አይተው እንዳላዩ ሆነው ሲታዘቡ ቆይተው፤ ሰብሉ በሚሰበሰብበት ግዜ በእሳት ማቃጠላቸውን የታዘበው ነዋሪው ህዝብ፤ የተራበ ህዝብ እያለን ለምን እህል እንዲቃጠል ተደረገ በሚል ምክንያት ብሶቱን በመግለፅ ላይ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስረድቷል።
በተመሳሳይ በአዲ ጎሹ ኣከባቢ በሚገኝ የእርሻ መሬት ሰሊጥ ዘርተው የከረሙ አርሶ አደሮች ከእርሻው ያገኙትን የሰሊጥ ምርት እየሰበሰቡ በነበርሩበት ሰዓት የዞን እና የወረዳ አስተዳሪዎች ያልተፈቀደ መሬት አርሳቹሃል በሚል ምክንያት ታማኝ ከድሬዎቻቸው በማሰማራት ከ1,300 ኲንታል የሰልጥ ምርት ከድሆች ዜጎች ነጥቀው እንደወሰዱባቸው ባለፉት የዜና ዘገባዎቻችን መግለፃችን ይታወቃል።