የትግራይ
ህዝብ በላዩ ላይ ይደርስ የነበረውን ብሄራዊ፤ መደባዊ ጭቆናና በየግዜው ስልጣን ላይ ከነበሩ ፊውዳላዊና ፋሽስታዊ ስርኣቶች ተላቆ
ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ስርኣት ለመገንባት፤ በአጠቃላይ በሁሉም ያገራችን ክፍል በተለይ ደግሞ በትግራይ መሬት ላይ የካቲት 11
/1967 ዓ/ም በህዝቡ ተሳትፎ የትጥቅ ትግል እንደተጀመረ ይታወቃል።
የህዝባዊ
ወያነ ሃርነት ትግራይ /ህ.ወ.ሃ.ት/ ትግል ከመጀመሪያው ጀምሮ ይዞት የተነሳው አላማ ጠባብ አመለካከት የተጠናወተው አስተሳሰብ
የተከተለ የትግል መንገድ ቢሆንም የትግራይ ወጣትና አጠቃላይ ህዝቡ ግን ከአስከፊው የፋሽስቶች ስርአትና አስተዳደር እንዲላቀቅ ከነበረው
ፅኑ ፍላጎት የተነሳ ድርጅቱ ውስጥ ትላልቅ ችግሮች እየተከሰቱም ቢሆን ትግሉን ማካሄድ ምንም አማራጭ ስላልነበረው ተሃህት ህወሃትን
ደግፎ ለመታገልና መስዋዕትነት ለመክፈል ተገዷል።
የትግራይ
ህዝብ የትግል ታሪክ የሃገራቸውን ሉኣላዊነት ላለ ማስደፈር ብለው የባእዳን ወራሪወችን በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ ጀግኖች ሰማእታት
የሆኑበትና በኋላም በህዝቡ ላይ እየተፈፀመ የነበረውን በደል አንቀበልም በማለት የፈፀሙት የጀግንነት ታሪክ ነው። በመሆኑም የበፊቶቹ
አርበኞች የጀግንነት ምእራፍ ጠብቆ በሀገሩ ውስጥ የተፈጠሩትን ፀረ ህዝብ ስርአቶች በማስወገድ ላይ የከፈለው መስዋእትነትም ወደር
አልነበረውም።
ነገር ግን
የትግራይ ህዝብ የሚወዳቸውን ልጆቹን መርቆ በመላክ፤ ላቡን አንጠፍጥፎና ተሰዶ ያገኘውን ንብረትና ሃብት በሙሉ አቅሙ ለትግሉ አበርክቶ፤
ቤቱና አርሶ የሚጠቀምበት መሬቱ ሳይቅር በናፓል ተቃጥሎበት፤ ባጠቃላይ ከ65 ሺ በላይ ሰማእታትና ከአንድ መቶ ሺ በላይ ኣካል ጉዳተኛ
ሆኖ አምባ ገነናዊውን የደርግ ስርኣት ከደምሰሰው በኋላ ጥቂት አመታት እንኳ ሳይጓዝ ከግምት ውጭ በሆነ መንገድ በላዩ ላይ ክህደት
ተፈፅሞበታል።
ይህ ለመጪው
ሰላም፤ የተሻለ ኑሮና ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለማስፈን ብሎ የማይተካ ህይወቱን የከፈለው ሃርበኛና ታጋይ ህዝብ መጨረሻ ላይ የት አለህ
የሚለው መንግስትና ለከፈለው መስዋእትነት ዋጋ የሚሰጠው ስርዓት አጥቶ በመታገሉ ምክንያት ክብር ተሰምቶት መኖር ሲገባው የተገላቢጦሽ
ሆኖ የድካሙና የመስዋእትነቱ አስተዋፃኦ ደመ-ከልብ ሆኖ እንዲቀር ቢፈረድበትም የመንበርከክ ባህል አልነበረውምና አሁንም ጠላቶቹን
ለማስወገድና ያለተመለሰውን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ ሲል ባገሩ በረሃ ውስጥ መሽጎ ትግል እያካሄደ ይገኛል።
በላዩ ላይ
የሚደርሰውን የመብት ረገጣና በደል አሜን ብሎ ተቀብሎ የማያውቅ ጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የሁልግዜ ምኞቱና ፍላጎቱ ሰላምና እድገት
የተረጋገጠባት አገር ማየት ቢሆንም አገሩ ውስጥ በተፈጠሩ ፀረ ህዝብ የሆኑ የህወሓት-ኢህአዴግ አመራሮች ምክንያት ግን ፍላጎቱና
ምኞቱን ማረጋገጥ አልቻለም ብቻ ሳይሆን ከትግሉ በፊት ከነበረው የኑሮ ደረጃ በባሰ መልኩ እንዲኖር የተፈረደበት አሳዛኝ ዜጋም ነው።
በዚህ ምክንያትም
ነው የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ ተቀብሎ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ /ት.ህ.ዴ.ን/ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ በማገናዘብና
ለውጥ ይመጣ ይሆን ከሚል የረጋ አስተሳሰብ ተነስቶ ግዜ ቢሰጠውም በወያኔ-ኢህአዴግ ስርና ስርአቱን እየመሩ ካሉ በግል ጥቅም አመለካከት
የበስበሱ አመራሮች ጉያ ሆኖ የህዝቡን ልማት ማረጋገጥና ዴሞክራስያዊ ስርአት ማስፈን እንደማይቻል ተገንዝቦ ትግሉን ማስቀጠል የቻለው።
ት.ህ.ዴ.ን.
ከ40 አመት በፊት የተመሰረተው የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ትግል የህዝቡን ጥያቄና ፍላጎት ያልመለሰ፤ ተጨባጭ የድርጅቱን
ክህደት አይቶ በማረጋገጡ፤ የድርጅቱ አመራሮችም የገቡትን ቃል ወደ ጎን ገፍትረው ወደ ራሳቸው ጥቅም በመግባታቸውና ግልፅ በሆነ
ፀረ ህዝብ አቋም ላይ ተዘፍቀው በማየቱ ትህዴን ይህንን ዛሬ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደርሰውን ህብረ ብሄራዊ ሰራዊት በማደራጀት ትግሉን ለማካሄድ የበቃው።
የትግራይ
ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ት.ህ.ዴን./ የወያኔ ስርዓት ለማደናገር ብሎ እንደሚናገረው ሳይሆን የካቲት 11 የጭቁኖች መብራት
ናት የሚለው ርካሽ መፈክር ምንም አይነት የብርሃን ጭላንጭል እንዳላመጣች፤ ይባሱን እንዳለፈው የክህደት ዘመን ፀረ ህዝብ ተግባራቱ
በባሰ እየቀጠለ እንደሚገኝና ዜጎቻችን ወደ ከፋ ችግር ገብተው ያሉበት ሁኔታ መሆኑን ያረጋግጥልናል።