Wednesday, January 21, 2015

በአብደራፊ ከተማ የሚገኙ የክልል ፖሊሶችና የፈደራል ፖሊሶች በሆቴል ገብተው የበሉበትንና የጠጡበትን ሒሳብ ሳይከፍሉ እየሄዱ መሆናቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በመረጃው መሰረት በአማራ ክልል አብደራፊ ከተማ የሚገኙ የታጠቁ የስርዓቱ  የክልል ፖሊሶችና  የፌደራል ፖሊሶች በትግራይ ተወላጆች በሆኑት ሆቴሎች በመግባት የበሉበትንና የጠጡበትን ሒሳብ ሳይከፍሉ እየሄዱ መሆናቸውን ከገለፀ በኋላ የተቋማቱ ባለቤቶች እየወረደባቸው ያለውን ግፍ ወደ ሚመለከታቸው አካላት አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም የሚሰጣቸው ምላሽ ወደ ሃገራችሁ ሂዱ እዚ ምን አላችሁ እያሉ እያባረሯቸው መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
  የክልሉ ባለስልጣናት በሁለቱ ክልል ህዝብ መካከል ግጭት እንዳይጠፋና ቂም እንዲኖር ሆን ብለው ትንኮሳዎችን እየሰሩ መሆናቸውን በመግለፅ የዚህም ምክንያት ደግሞ የሁለቱን ክልል ህዝብ ከፋፍለው የስልጣን እድሜያቸውን ለማራዘም የሚጠቀሙበት መላ መሆኑን በርካታ ታዛቢዎች በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ በስልጣን ላይ የሚገኘው አምባገነኑ የህወሃት ኢህአዴግ ስርዓት የሃገራችን ብሄር ብሄረሰቦች ተከባብረውና ተቃቅፈው በመኖር ላይ ናቸው እያለ በብሄር ብሄረሰቦች ስም ያከበረው በዓል ለማስመሰልና ለማታለያ እየተጠቀመ የእድሜ ስልጣኑን ለማስረዘም እያከናወነው መሆኑን ሊታወቅ ተችሏል።