Wednesday, January 21, 2015

በሁመራ ከተማ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ወገኖቻችን የገዥው መንግስት የደህንነት አባሎች ኮንትሮባንድ እየሰራችሁ ናችሁ በማለት እያፈኑ በመውሰድ እያሰቃዩአቸው መሆኑ ተገለፀ።



በሁመራ ከተማ በንግድ ስራ የተሰማሩ ዜጎች በስርዓቱ ተላላኪዎች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ  የኮንትሮባንድ ስራ ትሰራላችሁ በሚል እየታሰሩ እንዳሉ የገለፀው መረጃው  የመታሰሪያ  ምክንያታቸውም  ከትህዴን ጋር እየተገናኛችሁ ናችሁና ጉቦ ስጡን በማለት በልዩ ሁኔታ እየተሰቃዩ መሆናቸው ታውቋል።
  መረጃው ጨምሮም ታፍነው ከተወሰዱት በምሳሌነት ለመጥቀስ ጎይቶኦም የተባለ በሁመራ ከተማ ቀበሌ 03 ነዋሪ በኮንትሮባንድ ስራ ስለያዙት ጉቦ ስጠን ሲሉት ለጊዜው 15 ሺህ ብር  የከፈለ ቢሆንም እስካሁን  ባልታወቀ ቦታ አስረው ሰብዓዊነት በጎደለው ሁኔታ እያሰቃዩት እንዳሉና እንዲሁም ኪሮስ ገብረማሪያም የተባለ የቀበሌ 03  ነዋሪ   የሆነውን   አፍነው በመውሰድ ራያ አካባቢ ልዩ ስሙ ቃሴ በተባለው ቦታ ከበርካታ ወገኖች ጋር እየተሰቃየ መሆኑን ሊታወቅ ተችሏል።