በላዕላይ አድያቦ ወረዳ ምድረ ፈላሲ ቀበሌ
አዲ ሓመዶ የተወለደው ሓጎስ ለገስ የተባለ ግለሰብ በደህንነት ሃላፊዎች
ተመልምሎ የእነሱ አቀባባይ ሆኖ ሲሰራ ከቆየ በኋላ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በሚፈልጉት አካሄድ ሊሰራ ባለመቻሉ ምክንያት ከትህዴን
ጋር እየተገንኘህ ትተባበራለህ በሚል ፈጠራ ከመኖሪያ ቤቱ አፍነው እንዳጠፉት ምንጮቻችን የላኩት መረጃ አመለከተ።
መረጃው ጨምሮም እኒህ ባለስልጣኖች አንድ መምህር አርአያ የተባለ ዜጋ
ከትህዴን ጋር ትብብር አድርገሃል የትህዴን አባል ነህ በማለት በፍርድ
ቤት ከስሰው ባቀረቡበት ዕለት ከትህዴን ጋር ይገናኝ እንደነበር በደንብ
እንደሚታወቅ ሌላው ቀርቶ የስርዓቱ ታማኝ ስለሆንክ አይታወቅብህም
በማለት የምባይል ቁጥሩን አሳልፎ ለትህዴን እንደሰጠበት አስመስሎ እንዲመሰክር በላይ ጥላሁንና ልዑል የተባሉ ተላላኪዎች ለወረዳው
የፀጥታና የድህንነት ሃለፊ ተናግረው እሱ ግን በማላውቀው አልመሰክርም ስላላቸው ምስጥር እንዳይወጣባቸው በመፍራት እንዳጠፉት ታውቋል።