በመቐለ ከተማ
ልዩ ስሙ ስራዋት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሰፍረው የሚገኙት በ4ኛ ሜካናይዝድ የሚታወቁ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ቡድን አባል የሆነ አስር
አለቃ ዋጃ የተባለ ታህሳስ 28 ቀን 2007 ዓ/ም ሸዊት የተባለችውን
የአካባቢው ነዋሪ ሴት ሊደፍራት ሞክሮ እምቢ ስላለችው በጥይት ተኩሶ እንደገደላት ሊታወቅ ተችሏል።
አስር አለቃው
ገድሎ ሊሰወር ሲሞክር ነዋሪው ህዝብ ተባብሮ ሊይዘው ሲል ራሱን በራሱ ጥይት እንዳጠፋ የገለፀው መረጃው በወታደሮች ብልሹ ተግባር
የተቆጣው ነዋሪ ህዝብ ልጆቻችን በቀያቸው እንደፈለጋቸው መውጣት መግባት አልቻሉም በማለት በህፃንነት እድሜያቸው እየተዋረዱና እየተራክሱ
ስለሆነ የሚመለከተው አካል እነዚህን ወታደሮች ከአካባቢያችን ያስወግድልን ሲሉ በተጠቀሰው ዕለት
ከፍተኛ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማሰማታቸው ታወቋል።