በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ሽሬ ከተማ
ልዩ ስሙ ማይ መሳኑ በተባለው ቦታ ከሚገኘው ወታደራዊ መጋዝን ሃላፊዎች በርከት ያሉ ጥይቶችንና ሌሎች መሳሪያዎችን በሚስጥር ለመሸጥ
በወታደራዊ መኪና ወደ ጎንደር ሊያጓጉዙት ሲሉ እንደተያዙ ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ ገልፀዋል።
መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው ታሕሳስ 27 /2007 ዓ/ም በታርጋ ቁጥር
02506 ዋዝ የሆነችው ወታደራዊ መኪና ከተጠቀሰው ቦታ መሳሪያ ጭና ወደ ጎንደር በመጓዝ ላይ እያለች በዓዲ-አርቃይ እንደተያዘች
ከገለጸ በኃላ፣ የሚኪናዋ ሹፌር ፍቃዱ ንዋይ የተባለ ሲሆን። መሳሪያውን ጭኖ እንዲወስድ ያዘዘው ደግሞ ሻለቃ ጌታቸው በላይ የተባለ
እንደሆነ ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እያለ በኢህአደግ መከላከያ ሰራዊት ሃላፊዎች የሚካሄድ መሳሪያ
የመሸጥ ተግባር በሁሉም የሰራዊቱ ክፍሎች የተለመደ መሆኑን ከገለፀ በኃላ ይህ ደግሞ የሰራዊቱ አዛዦች በስርአቱ ላይ ያላቸው እምነት
ስለቀነሰ የግል ኑራቸውን ለማደላደል የሚያካሄዱት የስርአቱ ባለስልጣናት
መለያቸው ሆኖ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።