ምንጮቻችን ከከተማዋ እንደገለፁት ከፌደራል
ከፍተኛ ሃላፊዎች በመጡት የኢህአደግ ባለስልጣናት ከታህሳስ 22 እስከ 24 /2007 ዓ/ም በአካለ ወልድ ፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤት
የተካሄደው ስብሰባ ከደቡብ ወሎ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ ከ210 በላይ መምህራን ሲሆኑ የመሰብሰቢያቸው አጀንዳም መጪው ሃገራዊ፤
ክልላዊ ምርጫና የመንግስት ፖሊሲን ያቀፈ ሲሆን መምህራኖቹ ግን አስተያየታቸውን ሳይሰጡ በድምፀ-ተዓቅቦ እንደወጡ ታወቋል።
መረጃው ጨምሮ የስብሰባው ዝርዝር አጀንዳም ግንቦት 16 /2007 ዓ/ም በሚደረገው አስመሳይ ምርጫ ጊዜ ተማሪዎች በሌሎች አንድ አንድ ተማሪዎች ተታልለው
አመፅ እንዳያስነሱ ጥብቅ ክትትል እንዲያደርጉላቸው፤ ከዚህ አልፈውም ደግሞ ያለውን እንቅስቃሴ ለሚመለከታቸው አካላት መረጃ መስጠት
እንዳለባቸው የሚል ሲሆን መምህራኖቹ ግን ስማችሁን ሳትነግሩን ከየት የመጣችሁ ናችሁ እዚህ አንናገርም በማለት በዚህ የሁለት ቀን
የውይይት ስብሰባ ላይ ሃሳባቸውን ሳይሰጡ ተቃውመው እንደወጡና ሰብሳቢዎቹም በእፍረት አንገታቸውን ደፍተው ከአደራሹ እንደወጡ ለማወቅ
ተችሏል።