Saturday, January 17, 2015

የወልቅጤ ከተማ ነዋሪ ህዝብ በንፁህ የሚጠጣ ውሃና በሌሎችም የማህበራዊ ችግሮች እየተሰቃየ እንዳለ ምንጮቻችን ገለፁ።



    ምንጮቻችን ከከተማዋ እንደገለፁት በደቡብ ክልል የምትገኘው የወልቅጤ ከተማ ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ ንፁህ የሚጠጣ ውሃ ጠቅልሎ እንደጠፋ ከገለፀ በኋላ የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ በተደጋጋሚ ብሶቱን በፅሁፍ ወደ ከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ቢያቀርብም እንኳ እስከ አሁን ድረስ ግን መፍትሄ የሚሰጥ አካል በማጣቱ ለአንድ ወር ያህል በውሃ እጥረት እየተሰቃየ እንዳለ ታወቋል።
   ለችግሩ መፍትሄ የሚሰጥ አካል ያጣው የወልቅጤ ከተማ  ነዋሪ ህዝብ ገንዘብ እያዋጣ መኪና በመከራየት ከ100 ኪ/ሜትር በላይ የሚሆን ርቀት በመጓዝ ከስልኪ አምባ ወረዳና ወሊሶ ከተማ የሚጠጣ ውሃ እንዲያመጣ ተገድዶ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው በመጨረሻም የከተማዋ ነዋሪዎች አጋጥሞ ያለው  የውሃ እጥረትና ሌሎችም የማህበራዊ ችግሮች እንዲፈቱላቸው በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንዳሉ አስረድቷል።