በትግራይ ምእራባዊ ዞን፤ ፀገዴ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ሽፍቶች በስርአቱ ልዩ ሃይል ታጣቂዎች ላይ ጥቃት እያደረሱ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው
ሞላ ተስፋይ የተባለው ሽፍታ 10 ተባባሪዎቹን በመያዝ ማይ ደሌና ሰሮቃ በተባለው አካባቢ አድፍጠው በመጠበቅ 5 የስርአቱን ታጣቂዎች
መግደላቸው ተገለፀ።
ጥቃት በተካሄደበት አካባቢ ከተገደሉት የስርአቱ ልዩ ኃይል አባላት ታካሊ
አባተ፤ አለበል ኪዳነና ሌሎችም መሆናቸውንና ሽፍቶቹ ይህን እርምጃ እንዲወስዱ ያስገደዳቸው ዋነኛው ምክንያትም የስርዓቱ ታጣቂዎች በህዝቡ ላይ ሲያካሂዱት የቆዩት በደል ከግዜ
ወደ ግዜ እየባሰ በመሄዱ እርምጃውን እንደወሰዱት አንዳንድ ታዛቢዎች ከአካባቢው መግለፃቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።