Monday, January 12, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የኢህአዴግ ቡድን የጸጥታ ሃላፊዎች ከመስጊድ ንፁሃን ሰዎችን እየጠለፉ በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ።



ምንጮቻችን በላክሉን መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ የሚኖሩ የእስልምና ሃይማኖት  እምነት ተከታይ የሆኑ ወገኖቻችን ታህሳስ 25/ 2007 ዓ/ም የመውሊድ በዓልን ለማክበር እየተዘጋጁ በነበሩበት ግዜ ስርዓቱ ተቃውሞ እንዳያስነሱ ስስለሰጋ  በቦታው የፌደራል ፖሊሶችን በማሰማራት መስጊድ ውስጥ ሆኖው ፀሎት ሲያደርጉ ለነበሩ መእመናን በዱላ እየደበደቡ በበተንዋቸው ወቅት 8 የሚደርሱ  ንፁሃን ሰዎችም ከመስጊዱ እንደ ተጠለፉ ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው ጨምሮ የኢህአዴግ ካድሬዎች በህገ መንግስታቸው ውስጥ የደነገግቱን ሕግ በመጣስ በሃይማኖት ላይ እጃቸውን እያስገቡ መሆናቸውንና የስርአቱ ፖሊሶችና ወታደሮችም ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ መስጊድና ቤተክርስትያን ውስጥ በመግባት ንፁሃን ሰዎችን እየደበደቡ፤ እየጠለፉና ቦታውን እያራከሱት መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።