Thursday, January 1, 2015

በሸራሮ ከተማ በአነስተኛ ሸቀጣሸቀጥ ስራ ተሰማርተው የቆዩ ዜጎቻችን የከተማዋ አስተዳደሮች እቃዎቻቸውን ቀምተው እንዳባረሯቸው ተገለፀ።




   ከከተማዋ የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በሽራሮ ከተማ በንግድ ስራ ተሰማርተው ኑራቸውን እየመሩ ያሉ ወገኖች በተለይም ልብስና ሌሎችም ሸቀጣሸቀጥ ይዘው እየዞሩ የሚሸጡ አነስተኛ ነጋዴዎች በስርአቱ ተገደው ከልክ በላይ ግብር የሚከፍሉት ሳይበቃቸው ላባቸውን አፍስሰው ያፈሩትን ገንዘብና የገዙት የሸቀጣሸቀጥ ንብረታቸው ካላንዳች ምክንያት ወርሰው ከከተማዋ እንዳባረሯቸው ታወቀ።
  በተመሳሳይ አቶ ተኸስተ የተባለው የከተማዋ ነዋሪና የህንፃ መሳሪያ ባለቤት የሆነው ነጋዴ የአምስት ወር ግብር 101ሺ ብር ክፈል ተብሎ ስለተገደደ ይህንን ያህል ለመክፈል አቅም የለኝም ባለበት ግዜ የስርአቱ ካድሬዎች በአስገዳጅ ትከፍላለህ ብለው በማስቸገራቸው የከተማዋ ህዝብም የግብር አከፋፈሉ ዘረፋ ነው በማለት መመርያውን እንደተቃወሙት ለማወቅ ተችሏል።