Thursday, January 1, 2015

በአማራና በትግራይ ክልል ነዋሪዎች መካከል በህዝብና በሚሊሻዎች የተጀመረው ግጭት በስርዓቱ ልዩ ሃይል ታጣቂዎች እየተባባሰ መሆኑን ታውቋል።




   በአካባቢው የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለጹት። በአማራ ክልል ልዩ ስሙ ግጨው በተባለው ቦታ ላይ በህዝብና በሚሊሻዎች መካከል የተጀመረ ግጭት የስርዓቱ ልዩ ሃይል የተባሉ ታጣቂዎች እጃቸውን በማስገባት እንዳባባሱት ከገለፀ በኋላ። በሁለቱም ክልሎች ልዩ ሃይሎች በተካሄደ ግጭት  ከክልል አንድ ደብረ መኮነን የተባለ የጋንታ መሪ ከሶስት አባሎቹ ጋር የሞተ ሲሆን በርካታ ሲቪሎች  ከሁለቱም ክልል መሞታቸው ተገለፀ።
  ይህ ግጭት ሊቆም ባለመቻሉ የተነሳ  ሊያረጋጉ የመጡ የመከላከያ ሰራዊትም ቢሆኑ ውጤታማ ስራ ሊሰሩ ባለመቻላቸው ከታህሳስ 14 እስከ 18 2007 ዓ/ም ለተከታታይ 4 ቀናት በጎንደር ሁመራ መንገድ የሚተላለፉ የመጓጓዣ መኪናዎች ሰሮቋ በተባለው ቦታ ታግተው እንደሰነበቱ ለማወቅ ተችሏል።
   በተመሳሳይ ዜና  በሰሮቋ ከተማ ታህሳስ 20/ 2007 ዓ/ም  ሌሊት 3 የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ቡድን ታጣቂዎች ተገድለው እንዳደሩ ታውቋል።
 በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በስሮቋ ከተማ 3 የገዥው  ስርዓት   የታጠቁ ሃይሎች ከከተማዋ በምሽት በወጡበት ጊዜ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተኮሰ ጥይት እንደተገደሉ የገለፀው መረጃው ከተገደሉት መካከልም አሸናፊ ይደግ፦ እምባሁን ይመርና ይሳቅ ይመር መሆናቸውን  ከጠቀሰ በኋላ፥ የስርዓቱ የፀጥታ አካላትም የአርበኛ የተቃዋሚ ድርጅት አባሎች ናቸው በማለት ንፁሃን ዜጎችን እያፈኑ መውሰዳቸውን አስረድቷል።
  በአካባቢው የሚገኙ ካድሬዎች ከአርበኞች፦ ከግንቦት 7ና ከሌሎችም ተቃዋሚዎች የሚከፈት ተኩስ ስለሆነ ህዝብ መደናገር የለበትም በማለት እየቀሰቀሱ ሲሆን ይህ ግጭት በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል ስለተፈፀመ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የሚገኙ ካድሬዎችና የፀጥታ አካላት በሁመራ ከተማ ታህሳስ 20/ 2007 ህዝብ ሰብስበው ተቃዋሚዎች በላያችን ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት በጋራ እንከላከለው ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ታውቋል።