Friday, January 9, 2015

የሰሓርቲ-ሳምረ ወረዳ፤ ገረብ ግባ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደሮች መሬታቸውን በገዥው የኢህአደግ ስርአት ካድሬዎች በመቀማታቸው ምክንያት ከነቤተሰቦቻቸው ለርሃብ ተጋልጠው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከወረዳዋ ገለፁ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሳሓርቲ-ሳምረ ወረዳ ልዩ ስሙ ገረብ-ግባ በተባለው የእርሻ አካባቢ የሚኖሩ 25 አርሶ አደሮች ከሁለት አመት በፊት በስርአቱ ካድሬዎች መሬታቸው ሲወሰድ ካሳ እንዳልተከፈላቸው በሚመለከታቸው አካላት ውል የተፈፀመ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ግን የመሬት ካሳ ስላልተከፈላቸው ለችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ታወቀ።
    እነዚ አርሶ አደሮች ከክልሉ የውሃ ሃብትና መአድን ፅህፈት ቤት የወረዳው ሃላፊዎች በተገኙበት ውሉ እንደፀደቀ የገለፀው መረጃው ይሁን እንጂ በስምምነቱ መሰረት ተግባር ላይ ሊውል ባላመቻሉ ምክንያት እነዚህ ዜጎች ከነ-ቤተሰቦቻቸው ለማህበራዊ ችግር ስለ ተጋልጡ ታህሳስ 23 2007ዓ/ም ወደ ትግራይ ውሃና መአድን ሃላፊው  አለምሰገድ ገብረዋህድ በመሄድ ብሶታቸውን ባቀረቡበት ግዜ ሰለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለኝም በማለት ላቀረቡት ጥያቄ እንዳልተቀበለው ተገልጿል።
    የሳሕርቲ-ሳምረ የእርሻ ሃላፊዎች በበኩላቸው በአምባገነኑ ስርአት የደርሰባቸውን ችግር ለአርሶ አደሮች ጠበቃ መስለው ቢቀርቡም በተግባር ግን ከክልሉ ባለስልጣናት የተለየ አመለካከት እንደሌላቸው ምንጮቻችን ጨምረው አስረድቷል።