Friday, January 9, 2015

በቃፍታ ሁመራ የሚገኙ የአረና ፓርቲ አባላት በአካባቢው እያካሄዱት ባለው ቅስቀሳ ሙሉ የህዝብ ድጋፍ በማግኘታቸው ምክንያት ለስርዓቱ ካድሬዎች ወደ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንዳስገባቸው ተገለፀ።



ምንጮቻችን እንደግለፁት፣ በቃፍታ ሁመራ ወረዳ፤ ራውያን ቀበሌ የሚገኙ በርካታ የአረና ፓርቲ ወጣት አባላት ከሌሎች ነዋሪዎች ጋር በመሆን ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር የለም፤ ህዝብ በመሰረታዊ አላቂ ነገሮች እጦት እጅግ እየተሰቃየ ነው በማለት የተለያዩ ፓምፕሌቶችን በመበተንና በተለያዩ ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ እያካሄዱት ባለው የህዝብ ቅስቀሳ በወረዳው ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ እያገኙ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏ።
   የአረና ፓርቲ አባላት ለህዝብ ሰብስበው በስርዓቱ ካድሬዎች ተወሮ   ያለውን የሁመራን መሬት በሰፊው በማስረዳት ባጭር ጊዜ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ስላገኙ የወረዳው አስተዳዳሪዎችና የቀበሌ ሓላፊዎች በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተው እንደሚገኙና እኛስ ለዚህ ህዝብ ምን ብለን ነው ቅስቀሳ አድርገን ከጎናችን የምናሰልፈው በማለት ጭንቀት የወለደው ስብሰባ በሁመራ ከተማ እያካሄዱ እንደሰነበቱ ለማወቅ ተችሏል።