Tuesday, March 17, 2015

በአብደራፊ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ዜጎቻችን የካቲት 11 አስመልክተው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ በህወሃት የተዘጋጀው ፕሮግራም ተቃውሞ እንዳስከተለ ተገለፀ፣



የህወሃት 40 አመት የካቲት 11ን በተመለከተ የህወሃት ባለስልጣናት የሆኑ ካድሬዎች ወደ አማራ ክልል አብደራፊ ከተማ እንዲሄዱ በማድረግ የካቲት 10 በአብደራፊ ከተማ ለሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ ያቀዱት ዝግጅት የከተማዋ ነዋሪዎች የስርዓቱ አምባ ገነን ባለስልጣኖች በፈጠሩት በሁለቱ ክልሎች ልዩነት የከተማዋ ተወላጆች ትግራይ ውስጥ ሄዳችሁ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጉ እንጂ እዚህ በከተማችን ሰላማዊ ሰልፍ ማድርግ አትችሉም በማለት ታስቦ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን በከተማዋ የሚገኙ ምንጮቻችን አስታወቁ፣
   የህወሃት ባለስልጣናት በዚህ ተቃውሞ እጅግ እንደተቆጡ የገለፀ ይህ መረጃ በዚህም ምክንያት በከተማዋ ሃይለኛ ግርግር ስለተፈጠረ የአካባቢው የፀጥታ ሃላፊ ነጋ ተሻለ የተባለ የስርዓቱ ተላላኪም የተነሳው ግርግር ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዳይሄድ በመስጋት ታጣቂዎችን በአካባቢው ቢያሰማራም በአካባቢው አሁንም ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳይነሳ በከባድ ስጋት ላይ ገብተው እንደሚገኙ ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል፣