Tuesday, March 17, 2015

በአዲ ሃገራይ ልዩ ቦታ ዓዲ ተልዖም በተባለ አካባቢ ህብረተሰቡን እያሰቃዩ ባሉ ሚሊሻዎች ላይ የአካባቢው ህብረተሰብ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ ተገለፀ፣



በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ፤ በአዲ ሃገራይ አካባቢ፤ ልዩ ስሙ ዓዲ ተልዖም በተባለ ስፍራ የሚኖረውን ህብረተሰብ ሲያንገላቱ የቆዩትን ሚሊሻዎች ህዝቡ በላያቸው ላይ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝና እርምጃ ከተወሰደባቸው ሚሊሻዎች አንዱም ህዝቡ ዕለታዊ ስራውን እንዳያሳልጥ ስብሰባ ውጡ እያለ ነጋ ጠባ ሲያንገላታቸው የቆየው ተሾመ ተስፋይ የተባለ ካድሬ የካቲት 9/2007 ዓ.ም ምሸት ላይ በስለት ተገድሎ እንደተገኘ ለማወቅ ተችሏል፣
   የደረሰን መረጃ አክሎ እንዳስረዳው ይህ ፀረ ህዝብ የሆነው ሚሊሻ የተገደለበት ምክንያትም የስርዓቱ ካድሬዎች እስካሁን ለማወቅ ያደረጉት ጥረት ውጤት አልባ እንደሆነ ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል፣