Tuesday, March 17, 2015

የትግራይ ህዝብ ለተሰው ቤተሰቦች እርዳታ የሚውል ገንዘብ እንዲያዋጣ በህወሃት ኢህአዴግ አስተዳዳሪዎች እየተገደደ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ለሚገኝ የከተማና የገጠር ነዋሪ ህዝብ 40ኛው ዓመት የህወሃት ልደት በዓል ምክንያት በማድረግ የተሰውትን ቤተሰብ ለመርዳት በሚል እያንዳንዱ ቤተሰብ ገንዘብ እንዲያዋጣ በስርአቱ ባለስልጣኖች እየተገደደ መሆኑን የገለፀው መረጃው ይሁን እንጂ ህዝቡ ለአገራቸውና ለህዝባቸው ብለው እንደ ሻማ የቀለጡትን ሰማእታት ቤተሰቦች አቅማችን በፈቀደው ለመርዳት ጠቋሚ አያስፈልገንም በማለት የወረደውን ትእዛዝ እንደተቃወመው ተገለጸ፣
    መረጃው በማስከተል የህወሃት ኢህአዴግ ባለ-ስልጣኖች በየወረዳዎቹ እየዞሩ በካሃዲ አሰራራቸው ጠልቷቸው ያለውን የትግራይ ህዝብ ለማታለል ሲሉ የተሰውትን ቤተሰብና በትግሉ ውስጥ አካላቸውን የጎደሉ አርበኞችን ለማገዝ መንግስታችን ቆርጦ ተነስቷል በመጪው ምርጫ ላይ ብቻ ለህወሃት ኢህአዴግ ምረጡ እያሉ ቆይተው አሁን ደርሰው ሳይውሉ ሳያድሩ ለህዝቡ ገንዘብ አዋጡ ብለው በተናገሩበት ሰዓት በትግራይ ህዝብ ስም እየነገዳችሁበት ያሉትን ፋብሪካዎችና በንግድ ማእከላት የሚሰበሰበውን ገንዘብ የት እያስገባችሁት ነው? ልጆቻቸው ለተሰው ቤተሰቦች ያልሆነው ለማን ሊሆን ፈለጋችሁ? በማለት ህዝቡ ምሬቱን እየገለፀ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣