Tuesday, March 17, 2015

በአማራ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ከየካቲት 12/ 2007 ዓ/ም ጀምሮ የመብራት አገልግሎት መቋረጡን ከዞኑ ከተሞች የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



    ከከተሞች የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው ከደብረ ማርቆስ እስከ ቡሬ በአንድ መስመር መብራት የሚጠቀሙ ከተሞች ለ5 ቀናት ያህል መብራት የተቋረጠ ሲሆን ምርጫን በተመለከተ በቅርቡ የክልሉ ምክትል አስተዳዳሪ ብናልፍ አንዷለም በተለያዩ ዞኖች ባደረጋቸው ስብሰባዎች ላይም ነዋሪው ማህበረሰብ የመብራትን ጉዳይ ቢያነሳም የቴክኒክ ችግር ነው በሚል እየተቆራረጠ ላለው መብራት መፍትሄ ሊያስቀምጥ እንዳልቻለና ከዚህ ጋር በተያያዘም በመብራት የሚጠቀሙ የግል ድርጅቶች ለኪሳራ መጋለጣቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፣
    ይህ በእንዲህ እንዳለ በአማራ ክልል የምግብ አመጋገብ መዛባትና ችግር አለ በሚል የጠቅላላ ሴክተር መስሪያ ቤቱን ሰራተኞች በመሰብሰብ በመወያያ የቀረበውን የአመጋገብ ጉድለትና የአዮዲን ጨው እጥረት በሚል አጀንዳ ላይ የተደረገውን ውይይት ተሰብሳቢዎቹ የጨው አቅርቦት ብልሽት የመንግስት ችግር እንጂ የህዝቡ አይደለም ሲሉ እንደተቃወሙት መረጃው አክሎ  አስረድተዋል፣