Tuesday, March 17, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ ክፍለ ከተሞች እየተሰጠ ያለውን የከተማ ጤና ኤክስቴሽን ስልጠና ተግባራዊ መሆን አይችልም በማለት እየተቃወሙት መሆኑን ከአንዳንድ ሰልጣኞች የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



    ከሰልጣኞች የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በዲፕሎማ ደረጃ የበሽታ መከላከልና የጤና ማጎልበት የስራ ሂደት ባለቤትነት ለአጭር ጊዜ እየተሰጠ ያለውን የከተማ ጤና ኤክስቴሽን ስልጠና የአሰራር ፕሮግራሙ ከገጠሩ ለየት ስለሚል በዚች አጭር ጊዜ ስልጠና በተግባር ሊሰራ ስለማይችል ስህተት ነው በማለት የተቃወሙት ሲሆን የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህልም አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከምገኙ ዘጠኝ ጤና ጣቢያዎች የተወጣጡ ሃያ አንድ ባለሙያዎች በእጂጉ መቃወማቸውን ተገልጿል፣
    በሌላ በኩል ስልጠናውን ለመስጠት በሚል ሰበብ አበል ለማውጣት የሚሯሯጡ የጤና ጣቢያ ኦፊሰሮች በነፍስ ወከፍ ለሁለት ቀናት ብቻ ስልጠና እየሰጡ ከፍተኛ የህዝብንና የሃገርን ገንዘብ ያለህጋዊ ማወራረጃ እየዘረፉ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፣