Thursday, March 19, 2015

በአዊ ዞን ባንጃ ወረዳ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች በተደረገላቸው የ6 ወር የውጤት ተኮር የስራ ግምገማ ላይ በርካታዎች ማስጠንቀቂያና ዝቅተኛ ውጤት መሰጠታቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



መረጃው እንዳመለከተው በዞኑ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ፍቃዴ ድልነሳ መድረክ መሪነት “ቀጣይ የምርጫ ተልዕኮችንን ውጤታማ ለማድረግ የ6 ወር ውጤት ተኮር የስራ ግምገማችን ወሳኝ ነው” በሚል አጀንዳ። የካቲት 24/ 2007 ዓ/ም የባንጃ ወረዳ አጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞች ከፍተኛ ግምገማ መካሄዱ ታውቋል፣
በግምገማው ላይ መነሻውን የብአዴን ደጋፊነት በሚለው  አለመግባባት ከፍተኛ ጭቅጭቅ የታየ ሲሆን መረጃችሁ ወደ ውጭ ይወጣል በሚል ተገምግመው  ዝቅተኛ ውጤት የተሰጣቸው የግብርና ፅህፈት ቤት ባለሙያዎችና ሃላፊዎች የመልቀቂያና የቅሬታ ሰነድ አያይዘው ለወረዳው ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ ብርሃኑ አያሌው ካቀረቡት ሰራተኞች መካከል አቶ አዲሱ ፈቃድ፤ ወ/ሪት አማኔ፤ አቶ ወርቃየሁ ሙሉጌታ፤ አቶ አወቀና ሌሎችም ከ58 በታች የሆነ ውጤት የተሰጣቸው መሆኑን መረጃው  አክሎ አስረድቷል፣