በዞኑ የሚገኙ
የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች እንደገለፁት ከሆነ ከዚህ በፊት በፈቃደኝነት ከሁለት ጊዜ በላይ የቦንድ ግዥ ክፍያ
ከደመወዛችን ቆርጠን የለገስን መሆናችንን እያወቁ አሁን ከራሳችን ፍላጎት ውጪ ክፍያ እንድንፈፅም በማድረግ ህጋዊ ባልሆነ አካሄድ
ገንዘባችን ወደ ግድቡ ስራ መዋል ሲገባው አቶ ሙላት፤ አቶ ባይነሳኝና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በሆነው ባዘዘው ጫኔ የውስጥ አስተባባሪነት
ገንዘባችን ባክኗል ስለሆነም በህግ መጠየቅ አለባቸው ሲሉ አቤቱታ ማቅረባቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በሚመለከተው አካል ቀርበው
መጠየቅ አለባቸው የሚል ክስ ከቀረበባቸው የወረዳ ሃላፊዎች መካከል ይርጋ መንግስቱ የተባለ የጃዊ ወረዳ የብአዴን ፅህፈት ቤት ሃላፊ
ዘላለም ቢምረው የአንከሻ ወረዳ የፋይናንስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አይተነው ታዴ ከጃዊ ወረዳና ሌሎችም መሆናቸውን ታውቋል፣
በተመሳሳይ በአንከሻ ወረዳ የአዘና ትምህርት ቤት የወምበርና የመማሪያ መፅሃፍት
ችግር እንዳለባችው የትምህርት ቤቱ መምህራንና ተማሪዎች ባደረጉት ተደጋጋሚ ጥያቄ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ጌታየ ሁነኛው ከሃቅሜ
ውጭ ነው በማለቱ ችግሩ እልባት አጥቶ እየተጉላሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፣