Tuesday, March 10, 2015

በባዳ አካባቢ ልዩ ስሙ ናማ ጉቢ በተባለው ቦታ ህዝቡን ሲያንገላቱ የነበሩ የኢህአዴግ ካድሬዎች መገደላቸው ተገለፀ።



በቦታው የሚገኙት የአይን ምስክሮች እንደገለፁት በአፋር ክልል፤ ባዳ አካባቢ፤ ልዩ ስሙ ናማ ጉቢ በተባለው ቦታ ላይ የነበረው አርባ ዓሊ የተባለው ምክትል አስተዳዳሪ ሙሳ መሃመድ ከተባለው ታጣቂና ሌሎችም ጋር በመሆን በህዝቡ ላይ የተለያዩ ግፎች መፈፀማቸውን የገለፀው መረጃው የካቲት 23/2007 ዓ/ም  ሌሊት ላይ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ይዘው ሊወስዷቸው በሞከሩበት ግዜ ፈቃደኞች ሳይሆኑ በመቅረታቸው ምክንያት በቦታው ላይ እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው በመጨረሻ እነዚህ የስርዓቱ ካድሬዎች የነበሩት ሟቾች ስልጣናቸውን ተጠቅመው በህዝቡ ላይ የተለያዩ በደሎች ሲፈፀሙ መቆየታቸውና በታጣቂዎቹ ከመጥፎ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቅያ ተሰጥቷቸው መስማት ባለመቻላቸው በላያቸው ላይ እርምጃው መወሰዱ መረጃው አክሎ አስረድቷል።