Tuesday, March 10, 2015

በአሕፈሮም ወረዳ የሚገኙ የመዝብር ቀበሌ አስተዳዳሪዎች ህዝቡን ሰብስበው የመሬት ሽንሸና እንደሚያደርጉ ለነዋሪዎቹ ያቀረቡትን ሃሳብ በነዋሪዎቹ ተቃውሞ እንደአጋጠማቸው ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



    በመረጃው መሰረት በትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ አሕፈሮም ወረዳ፤ የመዝብር ቀበሌ አስተዳዳሪዎች የካቲት 24/ 2007 ዓ/ም ለአካባቢው ነዋሪዎች አዲስ የመሬት ሽንሸና ሊያካሂዱ መሆናቸውን ሃሳብ ባቀረቡበት ግዜ አስፈላጊ ጥናት ሳይደረግና ህዝቡ ሳያምንበት መካሄድ የለበትም በማለት የአካባቢው ህዝብ መቃወሙ ለማወቅ ተችሏል።
    በህዝቡ ተቃውሞ የተናደደው ጉዕሽ ምስግና የተባለው የቀበሌው አስተዳዳሪ ብትወዱም ባትወዱም መሬቱ ይሸነሸናል ምክንያቱም በእስልምናና በክርስትና አማኞች እጅ ያለው መሬት የተመጣጠነ አይደለም በማለት በሃይማኖት አሳቦ ህዝቡን ለማጋጨት ቢሞክርም ለረጅም ዓመታት ተባብሮና ተጋግዞ የቆየው ህዝብ ስለነቃባቸው ያሰበው ኢ-ፍትሃዊ ተግባሩ ሳይሳካ መቅረቱን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።