Wednesday, April 29, 2015

በኦሮሚያ ክልል የበደሌና ነቀምቴ ነዋሪዎች የኢህአዴግን ስርአት ብልሹ አካሄድ በመቃዎም ሚያዝያ 14 /2007 ዓ/ም የተካሄደውን ከባድ የሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፍ ወደ መከላከያ ሰራዊቱ እንዳይስፋፋ የስርዓቱ ባለስልጣኖች በውጥረት ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ።



    በመረጃው መሰረት በህዝቡ እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ በአካባቢው ተሰማርቶ ወደ ሚገኘው የኢህአዴግ ሰራዊት እንዳይስፋፋ የሰጉት ባለስልጣኖቹ ከሚያዝያ 12 /2007 ዓ/ም ጀምረው ማንኛውም ወታደር ከካምፑ እንዳይወጣና ከተመደበበት ክፍል ወደ ሌላ ክፍል እንዳይንቀሳቀስ እንዲሁም እንዳይገናኝ የሚከለክል ጥብቅ መመሪያ ወደ ሁሉም የሰራዊቱ ክፍሎች መተላለፉን ለማወቅ ተችሏል።
    የኢህአዴግ ስርዓት ከህዝቡ ተነጥሎ በመሳሪያ ሃይል ብቻ የቆመ በመሆኑ ይህ በህዝቡ ተነስቶ ያለው ተቃውሞ ተስፋፍቶ በሰራዊቱ ዘንድ ድጋፍ ማግኘት ከቻለ ለስርአቱ የመጨረሻ ውድቀት ሊሆን እንደሚችል የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።