በደረሰን መረጃ መሰረት በያዝነው ሳምንት ውስጥ
በሰሜን እዝ የህግ ሞያተኞችን አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት ላይ በኲሓ ከተማ ውስጥ 498 ወታደሮች በስነ ምግባር ጉድለት የታሰሩ
ሲሆን፤ 393 በወንጀል እንደታሰሩና ሌሎች ደግሞ በወንጀል ክስ ተፈርደው
በሌላ ቦታ ታስረው የተባረሩት ደግሞ 128፤ በጠቅላላ 1019 ወታደሮች መቀጣታቸውን ሪፖርቱ አመለከቷል።
ባሳለፍናቸው
ወራቶች ከአንድ እዝ ብቻ ይህን ያህል ወታደሮች መታሰራቸው ሰራዊቱ በመከላከያ ውስጥ እምነት እንደሌለው የሚያስረዳ እንደሆነና
የእዙ አመራሮችም ክፉኛ እያሳሰባቸው እንደሆነ የተገኘው መረጃ አስረድቷል።
በተመሳሳይ ከማእከላዊ እዝ የደረሰን ሪፖርት እንዳመለከተው ባለፈው ሳምንት
በገዢው ስርዓት መከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚገኙ የህግ ባለሞያዎችና የዲፓርትመንት አመራሮች የተገኙበት አራት ቀን የፈጀው ግምገማ
በርካታ የመገምገሚያ ነጥቦች እንደነበሩና በህግ ምክርና ወንጀልን በመከላከል ላይ በተገቢ መንገድ ስላልተሰራበት በርካታ ወታደሮች
ከድተው እንደጠፉና በተለያዩ የወንጀል ስራ እንደተሰማሩ ተገልጿል።
በመጨረሻ ግምገማው ከተጠቃለለ በኋላ የህግ ምክርና የዳታ ክፍል ኃላፊ የነበረው
መቶ አለቃ ፀጋየ የተባለ ወታደር እንዲታሰር መደረጉና ለቀሩት የህግ ባለሞያዎች ደግሞ በማስጠንቀቂያ እንዳለፏቸው መረጃው አክሎ
አስረድቷል።