ከስፍራው የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በኦሮሚያ
ክልል፤ ምስራቅ ወለጋ ዞን ጉትንና ሃሮ በተባሉ ከተሞች በሚገኙ አዳዲስና ነባር ከ6 በላይ የፍተሻ ኬላዎች መቋቋማቸውን የገለፀው
መረጃው። ከመጪው የይስሙላ ምርጫ ጋር በተያያዘ የህዝብ መኪኖች ለፍተሻ
በሚል ከ2 ቀናት በላይ እየቆሙ በመሆናቸው ተጠቃሚው ህዝብ በመንገድ ላይ ለረሃብና ተዛማጅ ችግሮች እየተጋለጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣
መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ፤ ጉትንና ሃሮ በተባሉ ከተሞች በህቡዕ የተደራጁ የታጠቁ የተቃዋሚ ሃይሎች ድርጅቶች
አሉ ከሚል የገዥው መንግስት ስጋት በተቋቋሙ የፍተሻ ኬላዎች በርካታ ዜጎችን በጥርጣሬ አይን እየታዩ እየታሰሩ መሆኑ ገልጿል፣