እንደምንጮቻችን ገለፃ በአማራ ክልል ምዕራብ
ጎጃም ዞን ፍኖተሰላም ከተማ ከሚገኘው ከፍተኛ ማረሚያ ቤት ውስጥ አንድ እስረኛ ሩጦ ማምለጡን ተከትሎ ከሚያዝያ 4 ቀን 2007
ዓ/ም ጀምሮ ከተማው ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው የፌድራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት እየተጠበቀ በመሆኑ ነዋሪው ህዝብ በነፃነት
እለታዊ ስራውን ለመስራት እንቅፋት እየሆኑበት መሆኑን የገለፀው መረጃው የጠፋውን እስረኛ ለመፈለግ በሚል በአቅራቢያው ከሚገኘው
ብርሸለቆ የወታደር ማሰልጠኛ ማዕከል የመጡ የሰራዊት አባላት የሚገኙባቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣
በተመሳሳይ
በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማም ከሁለት በላይ ሁኖ መቆም የተከለከለ ነው በሚል አድማ በታኝ ፌድራል ፖሊሶች ነዋሪውን
ማህበረሰብ እያሰቃዩት መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል፣