Sunday, April 26, 2015

በኦሮሚያ ክልል ነቀምት አርጆና በደሌ ከተሞች የገዥውን ኦህዴድ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ብልሹ አሰራር በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄዱ ተገለጸ።



     ይህ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል የነቀምት አርጆና የበደሌ ከተማ  ነዋሪዎች በስልጣን ላይ ያለውን አምባገነኑን የኦህዴድ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት በመቃወም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄዱ የገለፀው መረጃው አላማውም ፀረ ህዝቡ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ባሳደረባቸው ግፍና ጭቆና እንዲሁም ስራ አጥነት ተማርረው ስለተሰደዱና በሊቢያ ለተገደሉት ንፁሃን ኢትዮጵያዊያን ተጠያቂው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ነው በማለት ድምፃቸውን እንዳሰሙ ታውቋል።
   በዚህ በተካሄደው ተቃውሞ የሰጉ የስርዓቱ ባለስልጣናትም የበደሌን ከተማ ከንቲባ ከህዝብ ጋር ወግነህ ነዋሪዎች ተቃውሞ እንዲያካሂዱ አድርገሃል ለምንስ የፀጥታ አካላት ቀድመው እንዲሰማሩ አላደረግህም የሚሉና ሌሎችንም በማንሳት ከስራው እንዳስቆሙት የገለፀው መረጃው በአጠቃላይ በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት ማህበበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ካላመጣ ህዝብ ወደ ስደት ከመሄድ ሊታቀብ አይችልም ሲሉ ነዋሪዎች በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ እንደገለፁ ታውቋል።