Thursday, April 30, 2015

በደቡብ ወሎ ዞን ኩታብር በተባለው ወረዳ የሚኖረው ህዝብ በብአዴን/ ኢህአዴግ ካድሬዎች የተደረገለትን የስብሰባ ጥሪ እንቀበልም በማለት እንደተቃወመው ተገለጸ።



    በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ውስጥ  የሚኖረውን ህዝብ የብአዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎች መጋቢት 28/2007 ዓ/ም የምረጡን ቅስቀሳ ለማካሄድ ያደረጉለትን የስብሰባ ጥሪ አይመለከተንም በማለት እንደተቃወማቸው የደረሰን መረጃ አስታውቋል።
    የደቡብ ወሎ ህዝብ በብአዴን ኢህአዴግ ቡድን  ላይ ያለውን ጥላቻ በተደጋጋሚ በተቃውሞ መልክ እየገለፀ መምጣቱንና አሁን እያካሄደው ያለው ተቃውሞም የመጀመርያው እንዳልሆነና ከዚህ በፊትም ሲያካሂደው የነበረው አይነት ተቃውሞ እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።