ባገኘነው መረጃ መሰረት የህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች በትግራይ ክልል በባህላዊ
መንገድ በወርቅ ለቀማ ላይ ተሰማርተው ዕለታዊ ኑሮአቸውን እየመሩ የሚገኙ ንፁሃን ዜጎችን
በቁጥጥራቸው ስር አድርገው ለመያዝ እንዲመቻቸው ሰላማዊው
ህዝብ ወርቅ በሚለቀምበት ቦታ ላይ ወታደሮችን በመላክ ምንም አይነት ጥፋት ያልሰሩ ወገኖቻችንን እየያዙ እያሰቃዩዋቸው እንደሚገኙና
ይህን አይነት እርምጃ ለመውሰድ የተገደዱበት ምክንያት ደግሞ የትግራይ ህዝብ ወርቅ እንለቅማለን እያለ ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ
ንቅናቄ /ትህዴን/ እየተቀላቀለ ነው የሚል የተስፋ መቁረጥ እርምጃ
መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ህዝባችን የፈፀመው ወንጀል ሳይኖረው በኢህአዴግ
ወታደሮች ከህግ ውጭ በሆነ መንገድ እየታሰረ በመሰቃየት ላይ እንደሆነና በተለይ ወጣቱ ክፍል እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ እየተደበደበና
ኑሮውን እንዳይመራም ተቸግሮ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።