Tuesday, May 26, 2015

አዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የኢህአዴግ ስርዓት ታጣቂዎች ተከባ እየተጠበቀች እንደምትገኝ ታወቀ።



   የሃገራችን ርዕሰ ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 14 2007 ዓ.ም ጀምራ አምባገነኑ የኢህአዴግ ቡድን ባሰማራቸው ታጣቂዎች በጥብቅ እየተጠብቀች መሆንዋን የገለፀው ይህ መረጃው ታጣቂዎችም የክልል፤ የፌደራል ፖሊሶችና የመከላከያ ሰራዊት በአንድ ላይ በመሆን ለነዋሪው ህብረተሰብ አስቸጋሪ በሆነ ጥበቃ ላይ አስገብተውት እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ።
    በተጨማሪም ህዝብ በሚያርፍበትና በሚሰበሰብበት ቦታ ላይ ሁሉ ለሚያገኙት ሰላማዊ ዜጋ ለምን ተሰበሰባችሁ ግርግር ለማስነሳት ፈልጋችሁ ነው እያሉ እያንገላቱት የሚገኙ ሲሆን በዚህም  የተነሳም ነዋሪው ህብረተሰብ በከባድ ጭንቀት ውስጥ ገብቶ ቅሬታ ይዞ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
  ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢህአዴግ ስርዓት ደጋፊዎቼ ናቸው ላላቸው ታማኝ ታጣቂዎች መልምሎ የተለየ ስልጠና በመስጠት ልዩ ሃይል ብሎ በመሰየም በአዲስ አበባ ወልመራ በተባለ ቦታ በድብቅ አስፍሮአቸው እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገልፀዋል።
   ልዩ ስልጠና የወሰዱ ታጣቂዎች ዋነኛ ተልዕኮአቸው ስርዓቱ ተማኝ ሰላማዊና ነፃ የሆነ ምርጫ እንደማያካሄድ ስለሚታወቅ ህብረተሰቡ በምርጫ ጊዜ ለሚያነሳቸው አመፆች በአፈሙዝ ሃይል ለመበተን ተብለው በተጠንቀቅ ላይ የሚገኙ ታጣቂዎች እንደሆኑ የደረሰን መረጃ አመለከተ።