Wednesday, June 3, 2015

የጎንደር ከተማ ነዋሪ ህዝብ ኢህአዴግ ከ83% በላይ አሸነፍኩ በማለቱ የተነሳ ውጤቱን በመቃወምና መድረክን በመደገፍ አደባባይ በመውጣት ድምፃቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ታወቀ።



     የጎንደር ከተማ ህዝብ በኢህአዴግ ስርአት ላይ ከባድ ቅራኔ እንዳለው የገለፁት ምንጮቻችን በዚህ መሰረትም በጎንደር ከተማ ኢህአዴግ ሊመረጥ አይችልም፤ መድረክ ነው ሊመረጥ የሚችለው  በማለት ህዝቡ እየተናገረ ቆይቶ ግንቦት 16 2007ዓ/ም በተካሄደው የይስሙላ ምርጫ ኢህአዴግ 83% የህዝብ ድምፅ አግኝቻለሁ በማለት በከተማዋ የውጤቱን ወረቀት በመለጠፉ የተነሳ ህዝባዊ ተቃውሞ እንዳስነሳ ለማወቅ ተችሏል።
  የጎንደር ከተማ ነዋሪ ህዝብ መድረክን እንጂ ኢህአዴግን አልመረጥንም፤ የምርጫውን ኮሮጆ ራሳችሁ የስርአቱ ካድሬዎች ናችሁ የሞላችሁት በማለት ተቃውሞ ያካሄደ ቢሆንም የህዝቡን ድምፅ ሰምቶ መልስ የሚሰጥ የህግ አካል እንዳልተገኘ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።