Friday, June 12, 2015

ገዥው የኢህአዴግ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ህዝቦችን የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ድርጂቶች ዲሞክራሲያዊ ናቸው ብላችኋል በማለት ንፁሃን ዜጎችን እያሰረ መሆኑን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል።



   በአዲስ አበባ ከተማ ጀሞ በተባለው  አካባቢ  ግንቦት 7 እና ሌሎችም የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ድርጂቶች ዲሞክራሲያዊ ናቸው የሚል በራሪ ወረቀት መበተኑን ተከትሎ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የጀሞ አካባቢ ነዋሪ ግንቦት 22 ቀን 2007 ዓም ይህንን ንግግር አንተም ደግመህዋል ተብሎ የታሰረ ሲሆን በተመሳሳይ ግንቦት 15 ቀን 2007 ዓ/ም ቅዳሜ ምሽት ሁለት አውሮፕላን አብራሪዎች ሸራተን ሆቴል አምሽተው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ ምነው የምርጫው ዕለት ቀዘቀዘ ሰው የት ሄደ ብላችሁ ተነጋግራችኋል ተብለው በበርካታ የደህንነትና የፌድራል ፖሊስ ታጣቂዎች ታጅበው ወደ እስርቤት መወሰዳቸውን ምንጮቻችን ከቦታው ገልፀዋል።
   ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን የትግራይና የአዲስ አበባ ተወላጅ  ፓይለቶች ምንም የሰሩት ወንጀል ሳይኖራቸው በጥርጣሬ አይን በመታየት ግንቦት 17 ቀን 2007 ዓ/ም ካሳንቺስ ምድብ ችሎት ቀርበው በተወሰነ ውሳኔ መሰረት ምነው የምርጫው ዕለት ቀዘቀዘ ሰው የት ሄደ  ብለሃል የተባለው የትግራይ ክልል ተወላጅ ፓይለት 10ሺህ ብር እንዲከፍል የተወሰነ ሲሆን ሁለተኛው ምንም መልስ ባለመስጠቱ በነፃ ተሰናብቷል።