Friday, June 12, 2015

በደቡብ ጎንደር ዞን ወረታ ከተማ አንድ የመንግስት ታጣቂ ራሱን ጨምሮ የሁለት ዜጎችን ህይወት በማጥፋቱ ምክንያት በከተማው ላይ ከፍተኛ ሁከት ማስነሳቱ ተገለፀ።



በደረሰን መረጃ መሰረት በደቡብ ጎንደር ዞን የወረታ ከተማ ነዋሪ የሆነ በገዥው መንግስት ስር በአስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ ፅህፈት ቤት ይሰራ የነበረ ታጣቂ ካቢኔ ያለፈውን የምርጫ ሁኔታ አስመልክቶ  ከሚስቱ ጋር በተነሳ አለመግባባት ግንቦት 29 ቀን 2007 ዓ/ም ራሱን ጨምሮ ሚስቱንና የሚስቱን አጎት በክላሽ ኮፍ መሳሪያ መግደሉ የከተማዋን ነዋሪ ክፍኛ ማስቆጣቱን አንዳንድ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
    የወረታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት ሟች ሚስቱ ከዚህ በፊት የተቃዋሚ ፓርቲዎችን አመለካከት እንደምትደግፍና እንደመረጠች በተደጋጋሚ  ስትናገር ደስ እንደማይለው የተገነዘቡ ሲሆን ከገዳዩ ባለቤቷ ጋር ግን ምን እንዳጣላቸው እስካሁን የታወቀ ነገር ባይኖርም በወሰደው ራሱን የመግደል እርምጃ ግን ከገዥው መንግስት ብልሹ አሰራር የመነጨ ነው በሚል ከፍተኛ ቁጣቸውን እንደገለፁ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።