Saturday, June 6, 2015

የመቱ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ለመድረክ ተቃዋሚ ድርጅት ስለ መረጡ የስርአቱ ካድሬዎች ኮረጆ.ውን ነጥቀው መውሰዳቸው ተገለፀ።



በኦሮሚያ ክልል የመቱ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ግንቦት 16/2007 ዓ/ም በተካሄደው አስመሳይ ምርጫ አጋጣሚውን ተጠቅመው ሙሉ በሙሉ ለመድረክ ተቃዋሚ ድርጅት መምረጣቸውን የገለፀው መረጃው በዚሁ ሁኔታ የተደናገጡ የስርዓቱ ካድሬዎች ኮረጆውን ሰርቀው ለመውጣት በሞኮሩበት ሰዓት ተመሪዎቹ ድምፃችንን አትስረቁት ብለው ከግቢው እንዳይወጡ በከለከሉበት ሰዓት የስርዓቱ ታጣቂዎች ባስለቃሽ ጋዝና ቶክስ ተጠቅመው በኃይል መውሰዳቸውን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
     በዚሁ ለ 5 ግዜ በተካሄደው የስርዓቱ አስመሳይ ምርጫ ላይ የህዝብ ድምፅ የያዘውን ኮሮጆ የመስረቅና የመቀየር ተግባር በመቱ ዩንቨርስቲ ብቻ ሳይሆን በመላው የኢትዮጵያ አካባቢ የተፈፀመ  አስነዋሪ ተግባር መሆኑንን ለታዛቢዎቹና ፖለቲኮኞቹ መሰረት በማድረግ የተለያዩ የዜና አውታሮች ከመጀመርያውም አስነስተው በመግለፅ ላይ መቆየታቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።