Saturday, July 18, 2015

የሸራሮ ከተማ ነዋሪዎች ከገቢያቸውን የማይመጣጠን ግብር እንዲፍሉ እያሰገደዱት በመሆናቸው ለኪሳራ እንደተጋለጡ ታወቀ።



   በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ሸራሮ ከተማ በመንግስት የሚፈፀመውን የግብር አከፋፈል ያለ ምንም ጥናት እንዲከፍሉ በማድረግ የከተማዋን ነጋዴዎች ከልክ በላይ ግብር እንዲከፍሉ በመደረጋቸውና ለኪሳራ በመጋለጣቸው  ምክንያት በአስተዳደሩ ላይ ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሆኑ መረጃው አስረድቷል።
    ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ግብር እንዲከፍሉ ከተገደዱት የከተማዋ ነዋሪዎች ለመጥቀስ ያህል- አቶ ብርሃነ ሃይለ የህንፃ መሳሪያዎች ማከፋፈያ ባለቤት ከ2004ዓ/ም ጀምሮ ድርጅቱን ዘግቶት እያለ 80ሺ ብር እንዲከፍለ የተደረገ ዜጋ፤ አቶ ካሕሳይ ገብረኪዳን የብሎኬት ማምረቻ በለቤት 23ሺ ብር እንዲከፍል የተወሰነበት፤ አቶ ብርሃነ ሓድጉ የሸቀጣ ሸቀጥ ባለቤት ሲሆኑ እነዚህ ዜጎች መፍትሄ እንዲሰጣቸው በማለት ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታቸው ቢያቀርቡም ሰሚ አካል እንዳላገኙ መረጃው ከቦታው አስታውቋል።
    በተመሳሳይም የሸራሮ ከተማ ነዋሪዎች በአላቂ ነገሮች እጥረት እጅግ ተቸግረው እንደምገኙና በተልይም የምግብ ዘይት  ከገበያ ጨርሶ መጥፋቱና ለአንድ ኪሎ በርበሬ 180 ብር በመድረሱ ነዋሪዎቹ በከባድ የኑሮ ሁኔታ እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል።