Tuesday, July 21, 2015

በመቐለ ከተማ “የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ” በሚል በገዢው የህወሓት/ኢህአዴግ ስርአት የተጠራው ስብሰባ ያለ ምንም ፍሬ መበተኑን ታወቀ።



    እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት በመቐለ ከተማ የሰማእታት ሃወልት፤ ማዘጋጃ ቤትና አግአዚ መሰብሰቢያ አደራሽ ከሰኔ 20/ 2007ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 25/ 2007ዓ/ም ከሁሉም ሴክተር መስራቤቶችና የህወሓት አባላት የተሳተፉበት ስብሰባ ላይ እንደ አጀንዳ ተይዞ ወደ ስብሰባ የቀረቡት ያለፈውን አመት  “ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፀም” የሚል እንደሆነና የመድረኩ መሪዎች የ5ት አመት ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ በ3ቱም መሰብሰቢያ አደራሽ የነበረውን ህዝብ ከህወሓት አባላት ውጭ ፊስካን በመንፋት ተቃውሞውን እንደገለፀ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
    መረጃው በማከል ስብሰባው በመቐለ ከተማ ከንቲባና ዶ/ር ገብረዝጊ ኣብሄር እንደተመራና በተሳታፊዎች የቀረበውን የተቃውሞ ሃሳብም “ ተመዝግቧል የተባለ እድገት የት አለ?፤ ወጣቶች በሃገራቸው ሰርተው እንዲኖሩ መንገድ ለምን አይመቻችም?፤ ባለፈው 5ት አመት ብዙ የስራ አጥነት እንቀርፋለን ብላችሁ ነበር ለምን አልተተገበረም?፤ ሰዎች ፍትህ በማጣታቸው የተነሳ እየተሰቃዩ ናቸው የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች ቢያቀርቡም በመድረኩ መሪዎች ግን አጥጋቢ መልስ ስላልተሰጣቸው ሳይስማሙ ከአደራሹ እንደተበተኑ ለማወቅ ተችሏል።